photo 2025 10 07 10 53 55

በሀገሪቱ የሚገኙ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማህበራት በተገኙበት እንዴት ጠንካራ የዘርፍ ማህበራት እንፍጠር በሚል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡

በዚህ የምክክር መድረክ የልዩ ልዩ መንግስታዊ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በሀገሪቱ የሚገኙ የዘርፍ ማህበራት የቦርድ አመራሮች/ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በምክክር መድረኩ ታድመዋል፡፡
የምክክር መድረኩን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መላኩ አለበል በንግግር ያስጀመሩ ሲሆን በንግግራቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ነበሩ፡-

  • እንደመንግስት ሞጋች የሆነ እና ጠንካራ የዘርፍ ማህበራት እንዲፈጠሩ ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን ጠቅሰው የዕለቱ የምክክር መድረክም እንዴት ጠንካራ የዘርፍ ማህበራት እንፍጠር በሚለው ጉዳይ ላይ ለመመካከር የተዘጋጄ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
  • የዘርፍ ማህበራት በፖሊሲ አድቮኬሲ፣ በአቅም ግንባታ፣ የገበያ ዕድሎችን/ መዳረሻዎችን በማፈላለግ፣ ጥራት ያለው እና ተወዳዳሪ ምርት እንዲመረት ከማስቻል አንጻር አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል፡፡
    ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዘርፍ ማህበራት አንጻር የተሰሩ እና በዘርፍ ማህበራት ላይ በሚደረግ ድጋፍና ክትትል ወቅት ከተገኙ ውጤቶች በመነሳት በዘርፍ ማህበራት በኩል የታዩ ደካማ ጎኖች ጎላ ብለው በፕረዘንቴሽን የቀረበ ሲሆን በዘርፍ ማህበራት በኩል ስለ ማህበራቸው ውጤታማነት፣ አስተዋጽኦ፣ ቀጣይነት እና ቁርጠኝነት ዙሪያ ፕረዘንቴሽን እንዲያቀርቡ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት 3 የዘርፍ ማህበራት ተመርጠው እንዲያቀርቡ ተደርጓል የእኛ የዘርፍ ማህበርም ከ3 አንዱ ሆኖ በመመረጡ ዕድሉን መጠቀም ተችሏል፡፡
    ከምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
    በክቡር ሚኒስትሩ የተላለፉ ዋና ዋና መልዕክቶች

ከማህበራት በኩል የሚታዩ ክፍተቶች

  • የተቋቋሙበትን ዓላማ ታርጌት አድርገው እየሰሩ አለመሆናቸውን ጠቅሰው ነገር ግን ምሳሌ የሚሆኑ ዘርፍ ማህበራት መኖራቸውን አንስተዋል፡፡ የብረታ ብረት ፣ የኬሚካል ውጤቶች፣ የፋርማሲዩቲካል እና የሆልቲካልቸር ማህበራት ጠንካራ መሆን እንደሚቻል ያሳዩ ናቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህም ገና ብዙ ይቀራቸዋል ብለዋል፡፡
  • የመንግስትን ይሁንታ ከመጠበቅ መውጣት አለባችሁ፣ ከመንግስት ብዙ ትጠብቃላችሁ ሌላው ቀርቶ ባለሙያ እና ቢሮ የምትጠይቁ አላችሁ ያሉ ሲሆን መንግስት ካላጠነከረን አንጠነክርም ካላችሁ ተጎጂ የምትሆኑት ራሳችሁ ናችሁ ብለዋል፡፡
  • የተደራሽነት ችግር አለባችሁ አብዛኛዎቻችሁ አዲስ አበባ ላይ ባቻ ነው ትኩረታችሁ ፣
  • ተፅዕኖ የመፍጠር አቅማችሁ ውሱንነት አለበት፡፡ መፈታት ያለበት እና ችግር ነው፡፡ የዘርፍ ማህበራትን በቦርድ/ሥራ አስፈጻሚ አመራርነት የምትመሩ ተጽዕኖ ለመፍጠር እየተንቀሳቀሳችሁ ነው ወይ? ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
  • አዋጅ በማሻሻል ብቻ ጥንካሬን ማምጣት አይቻልም፡፡ አንዳንድ አመራሮች ስሙን/ማዕረጉን ብቻ የምትፈልጉ ናችሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
    ከመንግስት በኩል የታዩ ድክመቶች ብለው ያነሷቸው፡፡
  • በቂ ክትትልና ድጋፍ ከማድረግ አንጻር ክፍተት አለ ሊሻሻል ይገባዋል፡፡
  • ዘርፍ ማህበራትን empowered ከማድረግ አንጻር ይቀረናል በቀጣይ የሚሰራበት ጉዳይ ስለመሆኑ፣

በቀጣይ ምን እናድርግ? በሚል ከጠየቁ በኋላ የሚከተሉትን ሀሰቦች አንጸባርቀዋል፡፡

  • ያሉትን ማህበራት ማጠናከር፣
  • ጉባኤ እና ምርጫ እያካሄዳችሁ ልሆናችሁ ማህበራት ይሄንን ማድረግ፣
  • ከክልሎች ጋር መገናኘትና ትስስር መጀመር፣
  • ማሃበራት ሃብት የማፍራት ሥራ መስራት አለባችሁ፣
  • የ 5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቀድ እና የአንድ አመት እቅድ ከመንግስት የ10 ዓመት ዕቅድ ጋር በሚጣጣም መልኩ ማዘጋጄት አለባችሁ፣
  • ቢያንስ በዓመት 2 ጊዜ ቋሚ PPD ይኖረናል፣
  • ክፍተት ናቸው ያልናቸውን እንደ የቤት ስራ ወስደን እንደመንግስት እንሰራለ፣
  • የሚዲያ አድቮኬሲ እንደ ሚ/ር መስሪያ ቤትም በእናንተ በኩልም በትኩረት መስራት ይኖርብናል፣
  • በመንግስት ይሰሩ የነበሩ ነገር ግን በማህበር ሊሰሩ የሚችሉ ሥራዎችን አጥንተን በቀጣይ እንነጋገርባቸዋለን ለዛ ራሳችሁን ፈትሹ ዝግጅት አድርጉ ብለዋል፡፡
  • የዘርፍ ማህበር አባል ያልሆኑ ትላልቅ ድርጅቶች አባል የማሆኑት በግላችን ጉዳያችን እናስፈጽማለን ብለው ስለሚያስቡ ከሆነ በዘርፍ ማህበር በኩል ትላልቅ ድርጅቶች አባል እንዲሆኑ ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም በእኛ በኩል ከላይ ከተጠቀሱት የእኛን ዘርፍ ማህበር የሚመለከቱትን ሀሳቦች ወስደን የምንሰራባቸው ሲሆን ለተግባዊነቱ የእናንተን የውድ አባላቶቻችንን ድጋፍና ትብበር ከወዲሁ እንጠይቃለን፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *